የመውጫ ፈተናዉ በስኬት ተጠናቀቀ
Uploaded By: Super Admin
Posted On:
Feb 20, 2024
News
የመውጫ ፈተናዉ በስኬት ተጠናቀቀ
የካቲት 11/2016 ዓ.ም (ህ.ዉ.ግ.ዳ)
ከየካቲት 6-11/2016 ሲሰጥ የነበረዉ የ2016 ዓ.ም አጋማሽ መዉጫ ፈተናን ለ1326 እጩ ምሩቃንን መፈተን ታቅዶ 301 በተለያየ ምክንያት ያልተፈተኑ ሲሆን 1025 ተማሪዎችን ያለምንም እንከን እጅግ ስኬታማ በሆነ መንገድ መፈተን ተችሏል ሲሉ የዩኒቨርሲቲዉ አካደሚክ፣ ምርምር÷ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት እንዲሁም የዩኒቨርሲቲዉ ተወካይ ፕሬዝደንት ዶ/ር በድሉ ተካና የአካደሚክ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዶ/ር ድሪባ ገመቹ ከገለፁ በኋላ ለስኬቱ ሚና የነበራቸዉን ባለ ድርሻ አካላት በሙሉ አመስግነዋል፡፡ አንዳንድ ያነጋገርናቸዉ ተማሪዎችም ዩኒቨርሲቲዉ ለመዉጫ ፈተናዉ ተማሪዎችን ለማብቃት ከመጀመርያዉ ጀምሮ በሁሉም ረገድ ትልቅ ጥረት ሲያደርግ እንደ ነበረና ፈተናዉ እንደ ፈሩት ሳይሆን እጅግ በጣም ጥሩ ሆኖ እንዳገኙት ለሚዲያችን ገልፀዋል፡፡
Mattu University
Dedicated to serve the community!